Addis Ababa, Ethiopia

TradEthiopia በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የኦንላይን ኤክስፖ ሊያዘጋጅ ነው

TradEthiopia “አዲሱ የአለም አቀፍ ንግድ መንፈስ” በሚል መሪ ቃል ከህዳር 1-30 ፣ 2021 የመጀመሪያውን የኦንላይን ኤግዚቢሽን ያስተናግዳል። በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት የኤግዚቢሽን ዝግጅቶች ወደ ቨርቹዋል በመሸጋገራቸው ምክንያት ሀገራዊ ንግዶች ሰፊ ጥቅማ ጥቅሞችን እንዲያገኙ እንዲሁም ኢትዮጵያን ከሌላው ዓለም ጋር ለማገናኘት እንዲህ ዓይነቱን ክስተት ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኗል። ቨርቹዋል የንግድ ትርኢቶች ቀልጣፋ የኔትወርክ አቅም ፣ የወጪ ቅልጥፍና ፣ የተሻሻለ የተሰብሳቢዎች መጠን ፣ ጊዜ እና የኃይል ቁጠባ እንዲኖር በማድረግ አንጻር ጥቅማችቸው የጎላ ነው።

ኤክስፖው የውጭ ምንዛሪ ከማስገኘትና ዓለም አቀፍ የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቶችን ከማሳደግ አኳያ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደሚኖረው አዘጋጁ ትሬድ ኢትዮጵያ ያምናል። ከተሳትፎ ፣ ምዝገባ እና የ B2B ክፍያዎች የሚገኙ ገቢዎችም የኮቪድ ወረርሽኝ ከመከሰቱ በፊት ከMICE ቱሪዝም የሚገኘውን ተዛማጅ ገቢን በመተካት ጠንካራ ምንዛሬን ለማመንጨት አንድ መንገድ ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉ። በተጨማሪም ገዢዎች ፣ ሻጮች እና ባለሀብቶች አንድ ላይ ሆነው የንግድ ስምምነቶችን ለመወያየት እና ስምምነት ላይ መድረስ እንዲችሉ ፣ የንግድ፣ ግብይት እና የኢንቨስትመንት መረጃን ለማጋራት ምቹ መድረክ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህ የኦንላይን ኤክስፖ ላይ ለመሳተፍ በአጠቃላይ 8 የንግድ ዓይነቶች ተመርጠዋል። እነዚህ ዘርፎች ምግብ እና ግብርና ፣ ማሸጊያ ፣ ጨርቃጨርቅ ፣ የቤት ዕቃዎች ፣ ማሽነሪዎች ፣ ግንባታ ፣ የፀሐይ ሀይል ቴክኖሎጂዎች እና አውቶሞቲቭ ናቸው። በኤግዚቢሽኑ ከ 30 በላይ አገራት የመጡ ከ 600 በላይ የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ንግዶች ይሳተፋሉ። በተጨማሪም ከ 8000 በላይ ምርቶች እና አገልግሎቶች ከ 40,000 በላይ የሚሆኑ ጎብኝዎችን በመሳብ ይታያሉ። መድረኩ በመተግበሪያ ላይ ስለሚታይ እና እንደ የንግድ ካርድና፣ የ QR ኮድ ስካን፣ የማስተዋወቂያ ዕድሎች እና በብዙ መሰል መሣሪያዎች የታገዘ በመሆኑ ዝግጅቱ ለስፖንሰር አድራጊዎች የኢንቨስትመንት ጥቅሞች ላይ ታላቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

የኤግዚቢሽኑ ተሳታፊ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን እና አገልግሎቶቻቸውን በቀጥታ ማሳያ ፣ ምናባዊ ብሮሹሮች እና የቪዲዮ ቀረጻዎች ፣ የመስመር ላይ ኩፖኖች ፣ እና ሌሎች አቅርቦቶቻቸውን የሚያሳዩ ቴክኒኮችን ለመጠቀም እድሉ ይኖራቸዋል። ተሳታፊዎች በቀጥታ የጥያቄ እና መልስ ክፍለ-ጊዜዎች ፣ ምርጫዎች እና ውይይቶች ውስጥ በአካል ከመሳተፍ ጋር የተቀራረበ ልምድ ይኖራቸዋል። በኤግዚቢሽኑ ለሚሳተፉ ሰዎችም ፎቶ እና ፓስፖርት በማንሳት የሚከናወኑ ውድድሮች ይኖራሉ። ለምዝገባና ለተጨማሪ መረጃ ይህንን ይጫኑ

Leave a comment