Addis Ababa, Ethiopia

የጤና ዘይት በ 130% ምርቱን አስፋፋ ፣ 500 አዳዲስ ሥራዎችን ለመፍጠርም አቅዷል

54 ካፒታል  በጣም ተወዳጅ የሆነውን የምግብ ዘይት “ጤና ዘይት”  የማምረቻ ፋብሪካውን በዱከም ከተማ ውስጥ መስፋፋቱን አስታውቋል። አዲሱ ተቋም የኩባንያውን ምርት በ 130 % እንደሚጨምር እና ከ 500 በላይ አዳዲስ ሥራዎችን እንደሚፈጥር ተስፋ ተደርጓል። የተቋሙ አጠቃላይ ማስፋፊያ በ 2022 መጨረሻ ይጠናቀቃል ፤ ሥራ ሲጀምርም የአሁኑን ምርት በ400% ያሳድጋል ተብሏል። 54 ካፒታል በአገሪቱ ውስጥ የሚገኘውን የምግብ ዘይት እጥረት እየተቆጣጠረ የሚገኝ ሲሆን የሚያመርተው “ጤና” ዘይት ለጤናማ የአኗኗር ዘይቤ በጣም የሚመከር ነው።

የ 54 ካፒታል የቡድን ማኑፋክቸሪንግ ዳይሬክተር ኢዮኤል ሸዋንግዛው በዱከም ከተማ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት አዲሱ ፋብሪካ ሲጀመር “ጤና” ከመቼውም ጊዜ በላይ በከፍተኛ ጥንቃቄ እና በጥራት ይመረታል። ጤና ዘይት ማስፋፊያውን ማጠናቀቁም “ጤና በመጀመሪያ” ፤“በደንብ ተመገቡ ፣ በደህና ኑሩ”  የሚለውን የድርጅቱን መርሆችን ለማስቀጠል ያስችላል።

ጤና በገበያው ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ካላቸው የምግብ ዘይቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን፤ ብዙ አዳዲስ ሥራዎችን በመፍጠር ህብረተሰባችንን ጤናማ እንዲሁም ለአገሪቱ ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ የሚያደርግ ምርት ስላቀረብን በጣም ደስተኞች ነን።

“ጤና በገበያው ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ካላቸው የምግብ ዘይቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን፤ ብዙ አዳዲስ ሥራዎችን በመፍጠር ህብረተሰባችንን ጤናማ እንዲሁም ለአገሪቱ ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ የሚያደርግ ምርት ስላቀረብን በጣም ደስተኞች ነን” በማለት የድርጅቱ ማኑፋክቸሪንግ ዳይሬክተር ኢዮኤል ሸዋንግዛው ሃሳባቸውን አጋርተዋል። አዲሱ የምርት ፋብሪካ በዱከም ለሚገኘው ማህበረሰብ ከ 500 በላይ አዳዲስ ሥራዎችን ይፈጥራል። ጤና ዘይት ዝቅተኛ የስብ መጠን እንዲሁም ከፍተኛ ሞኖ እና ፖሊ ፋቲ አሲዶች የያዘ ሲሆን እነዚህም የሰውነት ኮሌስትሮል ኦክሲዳይዝ እንዳይደረግ ይከላከላሉ። በተጨማሪም በቫይታሚን ኤ እና ዲ3 የበለፀገ ነው።

54 ካፒታል በ 2013 የተቋቋመ አፍሪካ ተኮር የሆነ የሃብት አስተዳደር ድርጅት ነው። ኩባንያው እንደ ጤና ፣ 555 ፣ ኦውራ፣ ሼፍ ሉካ፣ እና አኳሴፍ ያሉ ታዋቂ ምርቶችን የያዘ 5 የፖርትፎሊዮ ኩባንያዎችን የሚያስተዳድር ሲሆን በኢትዮጵያም በኤፍኤምሲጂ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ የፋይናንስ ባለድርሻ ከሆኑት አንዱ ነው። ከ 54 ካፒታል ፖርትፎሊዮ ኩባንያዎች አንዱ ፣ ጤና  ዘይት በኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ታዋቂ ከሆኑ የምግብ ዘይት ምርቶች አንዱ ነው። ደረጃውን በጠበቀ የሶስት ጊዜ የማጥራት ሂደት በመጠቀም የጤናማ የምግብ ማብሰያ ሲሆን  ቀዳሚ ምርጫ ሆኖ ቀጥሏል።  


Leave a comment