Addis Ababa, Ethiopia

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ናይጄሪያ ኢኑጉ በረራውን ቀጥሏል

ጥቅምት 2 ቀን 2014 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ

ትልቁ የፓን አፍሪካ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከመስከረም 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ናይጄሪያ ኢኑጉ ሳምንታዊ የመንገደኞች አገልግሎቱን ቀጥሏል። በረራዎቹ የሚካሄዱት ረቡዕ ፣ አርብ እና ቅዳሜ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ናይጄሪያ ከሚበሩ አንጋፋ አየርመንገድ ውስጥ አንዱ ሲሆን በናይጄሪያ እና በተቀረው ዓለም መካከል የንግድ ፣ የባህል እና የቱሪዝም ግንኙነቶችን በማጠናከር ከ 1960 ጀምሮ አገሪቱን በማገልገል ላይ ይገኛል።

ከኢኑጉ የመጡ መንገደኞች በአፍሪካ ፣ በመካከለኛው ምስራቅ ፣ በእስያ ፣ በደቡብ አሜሪካ እና በአውሮፓ ወደሚገኙ በርካታ መዳረሻዎች የቀጥታ የበረራ እና በሰፊው የኢትዮጵያ ኔትወርክ ትስስር ይኖራቸዋል እንዲሁም ልዩ በሆነው ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ይደሰታሉ።

ናይጄሪያ በምዕራብ አፍሪካ አስፈላጊ ከሆኑት መዳረሻዎች አንዷ ነች ። ደንበኞቻችን የሚጠብቁትን ለማሟላት ምርቶቻችንን እና አገልግሎቶቻችንን በየጊዜው እያሻሻልን እንገኛለን፤ እናም ወደ ኢኑጉ የምናደርገው አገልግሎት  በተለያዩ የናይጄሪያ ክፍሎች የሚገኙ ደንበኞቻችንን ጋር ለመድረስ ወሳኝ ነው። አገልግሎታችንን ወደ ኢኑጉ እንደገና እንዲጀመር ለተደረገልን ትብብር የናይጄሪያን ህዝብ እና መንግስት እናመሰግናለን።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም እንዳሉት “ናይጄሪያ በምዕራብ አፍሪካ አስፈላጊ ከሆኑት መዳረሻዎች አንዷ ነች ። ደንበኞቻችን የሚጠብቁትን ለማሟላት ምርቶቻችንን እና አገልግሎቶቻችንን በየጊዜው እያሻሻልን እንገኛለን፤ እናም ወደ ኢኑጉ የምናደርገው አገልግሎት  በተለያዩ የናይጄሪያ ክፍሎች የሚገኙ ደንበኞቻችንን ጋር ለመድረስ ወሳኝ ነው። አገልግሎታችንን ወደ ኢኑጉ እንደገና እንዲጀመር ለተደረገልን ትብብር የናይጄሪያን ህዝብ እና መንግስት እናመሰግናለን።”

የኢትዮጵያ አየር መንገድ  በእ.ኤ.አ. በ 2013 በረራ ሲጀምር ወደ ኢኑጉ ለመብረር የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ አየርመንገድ ነበር። ኤርፖርቱ እድሳት እየተደረገለት ባለበት ጊዜ ለኢኑጉ አገልግሎት ለሁለት ዓመታት ተቋርጦ እንደነበርም ይታወቃል። አሁን ላይ በናይጄሪያ ውስጥ ከሚያገናኙን አራቱ ቦታዎች – ሌጎስ ፣ አቡጃ ፣ ካኖ እና ኢኑጉ ፤  መንገደኞችን በአምስት አህጉራት እና ከ 130 በላይ ወደሚሆኑ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች የመብረር ዕድል አግኝተዋል።

Leave a comment