Addis Ababa, Ethiopia

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአሜሪካው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሴበር ኮርፖሬሽን ጋር የገባውን ውል በ 110 ሚሊየን ዶላር አደሰ

አዲስ አበባ ፤ጥቅምት 2፣ 2014 ዓ.ም

የዓለም አቀፉን አየር ጉዞ ኢንዱስትሪን የሚመራው ዋና የሶፍትዌር እና የቴክኖሎጂ ምርቶች አቅራቢ የሆነው ሴበር ኮርፖሬሽን ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኩራት እና የአፍሪካው ትልቁ አየር መንገድ ከሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ  ጋር የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን የሚያረጋግጥ ለሰባት ዓመት የሚቆይ የ110 ሚሊዮን ዶላር ውል አድሰዋል። በስምምነቱ መሠረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ  የመንገደኞች አገልግሎት ስርዓት ሴበርሶኒክን የተሰኘውን ሶፍትዌር በመጠቀም ፣የገቢ ዕድሎችን ከፍ ለማድረግ እና ለተጓጓዦች ቀልጣፋ የአየር ማረፊያ ልምዶችን ለመፍጠር በማገዝ ሽያጭን እና አገልግሎትን በራስ-ሰር (Automation) እንዲሠራ ያስችለዋል። በተጨማሪም ፣ የሴበር ኢንተለጀንስ ልውውጥ የበለጠ በእውቀት ላይ የተመሠረተ የንግድ ውሳኔዎችን ለማድረግ እንዲረዳ በማሰብ የአየር መንገዱን ተሳፋሪ ተሞክሮ ለማሳደግ ይረዳል።

“የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከፍተኛ ተጽእኖ ቢያስከትልም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአቪዬሽን ታላላቅ የስኬት ታሪኮች አንዱ ሆኖ ቀጥሏል” ያሉት የሴበር ትራቭል ሶሉሽንስ እና EMEA ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዲኖ ጌልሜቲ ናቸው። በተጨማሪም “ኮቪድ -19 የአየር መንገዶችን ተወዳዳሪ ሆኖ የመገኘትን ጫና እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፍላጎትን አፋጥኗል ፣ እናም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ጠንካራ ተሸካሚ እንደመሆኑ ፣  በወረርሽኙ ምክንያት የመጣውን የገበያ ተለዋዋጭነት ተቋቁሞ መቀጠሉ ጥንካሬውን የበለጠ የሚያሳይ ነው” ብለዋል።

የተሻሻለው የስምምነት ውል የሴበር ቴክኖሎጂን ተገኝነትን (Availability) የሚያጠቃልል ሲሆን ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉዞ ሁኔታዎች በተሻሻለ የዋጋ አሰጣጥ ቀልጣፋ ምላሽ እንዲሰጥ የሚያግዝና ተጨማሪ ገቢን እንዲያገኝ ይረዳል። የሴበር ግሩፕ ኦፕቲማይዘር በግሩፕ የሚካሄዱ የመቀመጫ/አገልግሎት ማስያዣዎችን(reservations) የሚያሻሽል ነው።እነዚህ መፍትሄዎች በገበያ ፍላጎትና ውድድር ላይ የተመሰረቱ ምክሮችን (recommendations) ተወዳዳሪነቱን ይጨምራሉ።

“የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፣ ጠንካራ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያለው ሆኖ መገኘቱ ለስኬታችንና ታሪካችን ቁልፍ ሚና ይጫወታል” ያሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ናቸው።በተጨማሪም ዋና ሥራ አስፈፃሚው በማከል “ወረርሽኙ በጉዞ ኢንዱስትሪ ውስጥ ብዙ የማይታወቁ ነገሮችን ፈጥሯል ፣ የሳብሬ ቀልጣፋ ቴክኖሎጂ ከአዲሱ ገጽታ/ሁኔታ ጋር በፍጥነት እንድንላመድ ይረዳናል። የአቪዬሽን ጉዞ ማገገም ሲጀምር ፣ ትርፋማ እና ዕድገት ተኮር እንቅስቃሴዎች ላይ ማተኮር ተገቢና ወሳኝ ይሆናል። ከሴበር ጋር ያለን የቴክኖሎጂ አጋርነት የአሠራር ቅልጥፍናን በማዘመን ወደ ዘመናዊነት የምናደርገውን ጉዞ ያፋጥንልናል” ብለዋል።

የሳብሬ ጠንካራ የጉዞ አጋዥ ቴክኖሎጂ አስተማማኝነታቸው የተጠበቀ መፍትሄዎችን ለአየር መንገዶች ፣ ኤጀንሲዎች እና ሆቴሎች ይሰጣል። ድርጅቱ በጉዞ ኢንዱስትሪው ውስጥ ፈጠራን ለማፋጠን ቁርጠኛ ነው። የብዙ ዓመታት የቴክኖሎጂ ልምዱ የጉዞ አገልግሎትን ለማዘመን የሚያስፈልገውን ቅልጥፍና ፣ ልኬት እና መረጋጋት ይሰጣል። ይህም ሴበር ኮርፖሬሽን ለግል ጉዞ አዲስ የገቢያ ቦታ ለመፍጠር ያለውን ራዕይ አንድ እርምጃ ይወስደዋል።            					

Leave a comment